ስለ እኛ/About us

aapologo 200

የዐማራው ጥያቄ የመኖር ወይም ያለመኖር ጥያቄ ነው። የመኖር መብቱን ማንም ሊንፍገውም ሊሰጠውም አይችልም። መኖር መቻል ማንም የማይነካበት ተፈጥሮአዊ መብቱ ነው። ኢትዮጵያ አገሩ ስልሆነች ዐማራው የማይኖርበት ክፍለ አገር የለም። ባለበትና በሚፈልግበት ቦታ ሁሉ የመኖር መብቱን ማንም ሊነካብት አይገባም። የመኖር መብቱን በሠላም ማስከበር ካልቻለ አቅሙን በሙሉ መጠቀም ተፈጥሮአዊ መብቱ ነው።

በትግራይና በኤርትራ ትግሬዎች የተመሰረተው ኢሕአዲግ በሚል ስያሜ የሚታወቀው ፋሺስታዊ አገዛዝ በኢትዮጵያ ሕዝብ ጫንቃ ላይ ከተፈናጠጠ ጊዜ ጀምሮ ፤ በተለይ ላለፉት ሀያ አምስት ዓመታት፣ ከሌሎች ገዳይ ጎጠኞች ጋር በማበር በዐማራው ነገድ ላይ የፈጸሙት የዘር ማጥፋት፣ ዘር ማጽዳትና አዲስ ትውልድ እንዳይኖረው የማምከኛ መርፌ ሴቶችን መውጋት የመኖር መብትን መንፈግ ነው።

ከዚህ የዘር የማጥፋት ዘመቻ የተረፈው ዐማራ፣በገዛ  አገሩ የሚደርስበት ወከባ ዘር ከማጥፋት የማይተናነስ ሌላው በዐማራው ላይ ያነጻጸረ ዘመቻ ነው። ዐማራው የመማርም ሆነ የመስራት እድልና የህክምና ግልጋሎት ተነፍጎታል። ከቢሮክራሲውና ከንግድ መስኮች እየታደነ ይባረራል። በቀዬው ምንም ዓይነት የኢኮኖሚ እድገትና መሻሻል እንዳይኖር ታቅቧል። የዐማራ ወጣት ሴቶች በሴትነታቸው ብቻ እንዲሰማሩ ይገፋሉ። ሥራ ፍለጋ በአረብ አገር የተሠማሩት ወጣት ሴቶች መብታቸውን የሚያስከብርላቸው መንግስት በማጣታቸው ምክንያት ግፍ ተሸካሚ ሆነዋል። በያለበት የተገደሉትም ደማቸው ደመከልብ ሆኖ ቀርቷል።

በዐማራው ነገድ ላይ የደረሰውንና በመድረስ ላይ ያለውን እልቂት፣ግፍና በደል በመቃወም የየትኛውም አመለካከት ተከታይ ድርጅትም ሆነ ቡድን ድምጹን ያሰማ ወይንም ወግናዊነቱን የገለጸ የለም። ለሰብዓዊ መብት በሚል እንኳን ከተበዳዩ የወገነ አንድም ደርጅት አልታየም።

በመሆኑም የዐማራው ነገድ እራሱን ከእልቂት ለማዳን ቁጥሩም አቅሙም አለው። የትግሉን ስፋት፣ አቅጣጫና ግብ ነድፎ ከፋሺስቱ የትግሬ የጥፋት አገዛዝና ከገዳይ አባሮቹ እራሱን ለመከላከል፤ ታላቁ መሪና ሰማዓቱ ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ የሞቱለትን ዓርማ አንግቦ፤ የመላው ዐማራ ሕዝብ ድርጅትን መስረቶ፤ በባለቤት ወገኑን ለመታደግ ቆርጦ ተነስቷል።

ዐማራው ከዳር እስከዳር መነቃነቅና ትግሉን የማቀናጀት ኃላፊንት አለበት። መዐሕድን መቀላቀልና መደገፍ ይጠበቅበታል። የዐማራው በአንድነት መነቃነቅ እንኳን የትግሬ ፋሺስትን ይቅርና የጣሊያን ፋሺስትንም ከጀግና ኢትዮጵያን ወገኖቹ ጋር በመሆን አሳፍሮ መልሷል።

ዐማራው በተባበረ ክንድ የመኖር መብቱን ያስከብራል!!

በሠላምና በሰለጠነ ስርዓት እድገቱን ይቀጥላል!!