ከታሪክ መዝገብ – ለመሆኑ አማራ ማነው (ኀይሌ ላሬቦ)

haile-lareboዛሬ በሥልጣን ላይ ያለው የወያኔ መንግሥት ዐማራ በተባለው ኅብረተ-ሰብላይ ብዙ ግፍና ዐመፅ እንደፈጸመና እንዳስፈጸመ በገፍ ይነገራል። በኅብረተሰቡ ላይ ተፈጸሙ ከተባሉት ድርጊቶች አብዛኞቹ በሥዕል የተቀረጹ፣ለሰው መብት በቆሙ ባስተማማኝ ብሔራዊና ዓለም-ዐቀፍ ድርጅቶች ከነማስረጃቸው የተጠናቀሩ፣ እሙን በሆኑ ያይን ምስክሮች የተደገፉ ስለሆኑ ማስተባበሉ ከመደናቈርና የአተካራ ግብግብ ከመግጠም ውጭ ሌላ ፋይዳ ያለው አይመስለኝም። የግፎቹ ኢሰብኣዊነትና የፈጻሚዎቻቸውም አውሬነት ለሚሰማ ሁሉ ከመዘግነን አልፎ፣ ሰው ሁኖ መፈጠሩን ራሱን የሚያስጠላ ከመሆኑ የተነሣ፣ ልቦና ያለው ተመልካችም ሆነ ሰሚ፣መንግሥት ነን ባዮቹ የወያኔ ገዢዎች በጀርመንና በኢጣሊያን ምድር ከታዩት ከናዚና ከፋሽስት መንግሥታት መሪዎች በምን ይለያሉ ብሎ ለመጠየቅ ይገደዳል። Read in PDF

Share this post