ስንደግፍ አማራውን ማዘናጋት ሊሆን አይገባም !! ከቋራው አንብሳ

ስንደግፍ አማራውን ማዘናጋት ሊሆን አይገባም !!
ከቋራው አንብሳ
ጀግናው የወልቃይት ጠገዴና ጠለምት ሕዝብ ለአማራዊ ማንነቱ ከባድ መሰዋዕትነት እየከፈለ ነው።
የወለቃይት ሕዝብ የተፈጠረበትን ትውልድ ቦታ በወራሪወች ተቀምቶ የሱ ያልሆነ ማንነት በላዩ ላይ
ተጭኖበታል።የተጫነበትን የግፍ ቀንበር ለመስበር ጥያቄውን እንዲአነሳ ተገዷል። የጥያቄው መነሻ እንዲያው
ባጋጣሚ ለሳምንት የፖለቲካ ሞቅ ሞቅ ተብሎ የቀረበ አይደለም። ይልቁንም ጥልቅና ስር የሰደደ የአማራዊ
ማንነቱና የህልወናው መታወቂያ ስለሆነ ነው። ለጥያቄው ምላሺ ማግኘት ከሚገባው በላይ ዋጋ ከፍሎበታል
እየከፈለም ነው። በወራሪ ትግሬወች የተቀማውን አማራዊ ማንነት ለማስመለስ ከ 36 አመታት በላይ
ጭፍጨፋ ተፈፅሞበታል አሁንም እደቀጠለ ነው። ጥያቄው መልስ እስካላገኘ ድረስ መላውን አማራ ህዝብ
በማስተባበር ትግሉን አጠናክሮ ገፍቶበታል። ሰሞኑን በጎንደር ክፍለሐገርና በመላው አማራ ሕዝብ
በመቀጣጠል ላይ ላለው የነፃነት ሰደድ መለኮስ ያመላክተው እውነታ ቢኖር ይኽንኑ ሐቅ ነው። አቀበቱን
አውጥቶ አፋፍ ላይ ላደረሰን ለዚህ ታላቅ ህዝብ ምስጋና ይገባዋል ካሁን በሗላ የመላው አማራ ሕዝብ ጉዳይ
ነው እንጅ የሱ ብቻ ተደርጉ ሊታይ አይገባውም። ነገርን ነገር ያነሳዋልና ሰሞኑን የተደሰተው መላው አማራ
ህዝብ የመኖሩን ያህል አንገቱን የደፋም፤ አይአፋር የሆነም፤ የደነገጠም፤ ጮሌ ነጣቂም አልጠፋም ከዚህ
አንፃር ትዝብታችን ለመግለፅ ክስተቶች አስገድዶናል።ስንደግፍ አማራውን ማዘናጋት ሊሆን አይገባም !!…….pdf

Share this post