አሸባሪው ማነው? (ከቋራው አንብሳ )

ጉድ በል አገሬ የወልቃይት ጠገዴና ጠለምት ሕዝብ ያነሳው የአማራ ማንነት ጥያቄ ከመጀመሪያው እስከ
አሁኑ ደቂቃ ድረሰ ህጋዊ መብቱን ተጠቅሞ ነው። እራሱም ወያኔ በሚገባ ያውቀዋል። የአማራ ማንነት ጥያቄ
አስተባባሪወቹም የትውልድ ዋና ከተማቸው በሆነችው ጎንደር ተቀምጠው ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንግድ
ጉዳያቸውን ይከታተሉ ነበር። እብሪተኛው የትግራይ ገዠ አባይ ወልዱ የኮሚቴውን አባላት ማጥፋትና አፍኖ
መውሰድ ስለፈለገ የጦር መሳሪያ የታጠቀ ልዩ አፋኝ ቡድን ከትግራይ አዘጋጅቶ ጎንደር ከተማ ውስጥ አስርጎ
በማስገባት በደረቅ ሌሊት የኮሚቴ አባላቱ በሚኖሩባቸው ቤቶች አፈናውን ጀመረ። የኮሚቴው አባላት እጅ
ንዲሰጡ በራፍ እንዲከፍቱ ይጠየቃሉ። ነገር ግን ጠርጣራወቹ የኮሜቴ አባላት በሌሊት በራፍ ክፈቱልን
የምትሉት እናንተ እነማናችሁ እኛ ሰላማዊና ህጋዊ ሰወች ነን ችግር ካለ ደግሞ ሲነጋ ልንጠየቅ ይገባል እንጅ
እንዴት አሁን ክፈቱ ትሉናላችሁ በማለት ለአፋኝ ቡድኑ ጥያቄ ያቀርባሉ ስሚ ግን አላገኙም። አፋኙ ቡድኑ
በር ሰብሮ ለመግባት ማስገደድ ጀመረ። በዚህ ሁኔታ የታፈኑት የኮሚቴ አባላት እስካሁን ድረስ ያሉበት
አይታወቅም። በኮሎኔል ደመቀ ዘውዴ መኖሪያ ቤት ግን ለየት ያል ጉዳይ ተፈጠረ በራፍ ለመክፈት ፈቃደኛ
ያልሆኑት ኮሎኔል ደመቀ በራፉቸውን ለመስበር የሚታገለው አፋኝ ቡድን መሳሪያውን ሲአንቀጫቅጭ
ሰሙት። እጅ ለመስጠት ፈቃደኛ ካለመሆናቸውም በላይ እነማን እንደሆኑም ተገነዘቡ። ጀግናው ኮሎኔል
ደመቀ በራፋቸውን ሰብሮ ለመግባት ይታገል የነበረውን አፋኝ ቡድን ተራ በተራ አነጠፉት ይህ የተኩስ ድምፅ
በከተማው ተሰማ ስላማዊው ህዝብ ተነሳ ወደኮሎኔሉ መሮሪያ ቤት አመራ በሕይወት ስላገኛቸው ደስታውን
በመግለፅ ዙሪቸውን ከቦ ማንም መሳሪያ ያነገተ እንዳይጠጋቸው ማዕበል ነው በተሰኘው ህዝባዊ ድምፁ
ለኮሎኔሉ ደህንነት መጮህ ጀመረ። ከህዝቡ ከበባ በሁላ የደረሱት የከተማው ሹምና የብአዴን አመራሮች
ሕዝቡ የከበባቸውን ኮሎኔል ለማነጋገር የህዝቡን ፈቃድ ጠየቁ ሕዝቡም ኮሎኔሉ ሕጋዊ ሰው መሆናቸውን
ያውቃልና ለደህንነታቸው አስተማማኝ ነው ብሎ የገመተውን አማራጭ አቀረበ። የከተማው ከንቲባ ተረክበው
ተገቢ በሆነ ቦታ እንዲቀመጡ ተስማምቶ እስካሁን ድረስ በከተማው ከንቲባ እጅ ይገኛሉ:፡ ዘግይቶ በደረሰኝ
ሪፖርት መሰረት ለፍርድ እንደሚቀርቡ የሚጠቁም መረጃም አለ ጉድ እኮ ነው።አሸባሪው ማነው(1)……read in pdf

Share this post