ግልፅ ደብዳቤ ለክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ

ግልፅ ደብዳቤ ለክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ፤
የህወሓት ግንባር ላለፋት 27 ዓመታት በኢትዮጵያ ህዝብ ጫንቃ ላይ ጭኖት የነበረው በዘር ላይ የተመሰረተ የግፍ ፣ የመከራና የጭቆና ስርአት በህዝብ ላይ ከፍተኛ ጉዳት አስከትሏል ፤ የአገራችንንም ሉዐላዊነት አስደፍሯል ። ከአራት ወራት በፊት በእርስዎ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር እና በትግል አጋሮችዎ የተጀመረውን የለውጥ እንቅስቃሴ በተስፋ ሰጭነቱ ፣የመላው አማራ ሕዝብ ድርጅት (መዐሕድ) የለውጡ እንቅስቃሴ አጋር በመሆን በወቅቱ የድጋፍ መግለጫ ማውጣቱ ይታወሳል ። ሆኖም እስከአሁን ድረስ የአማራውን ህዝብ በተመለከተ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚፈፀሙት የፖለቲካ እንቅስቃሴና ተግባራት የአብሮ መኖራችንን ሠላም የሚያደፈርሱ ከመሆናቸውም በላይ፣ በአማራው ህዝብ ላይ የህይወት መጥፋትና የንብረት ውድመት ኪሳራዎች አስከትለዋል ።
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ፣
እርስዎ ስልጣን ከያዙ ጀምሮ ፣ የአማራው ህዝብ በቤኒሻንጉል ፣ በአሶሳ ፣ በወለጋ አሰቃቂ ግድያዎች የተፈፀሙበት ሲሆን ከሞት የተረፋትም በጅምላ ከይዞታቸው ተፈናቅለው እንዲሰደዱ ተደርገዋል ። ይህ ፀረ ህዝብ እኩይ ተግባር ከህወሓት አገዛዝ ያልተናነሰ የአማራውን ዘር ለማጥፋት የተፈፀመ ወንጀል ነው። መላው የአማራ ሕዝብ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን የጀመሩትን የለውጥ መንፈስ በመቀበል ፣ ስኬታማ ይሆን ዘንድ ድጋፉን በተለያየ መንገድ ሲገልጽ የቆየው፣ ለደረሰበት ግፍና መከራ የእርስዎ አስተዳደር ሚዛናዊ መፍትሄ ይሰጡታል ብሎ በማመንም ጭምር ነበር ። ሆኖም እርስዎ የሰጡት ኢትዮጵያዊነት ተስፋ እንደ ጠዋት ጤዛ ተኖ ፣ ዛሬ ለአማራው ህዝብ ከበፊቱ የግፍ አገዛዝ ባልተለየ ሌላ የመከራና የስቃይ ዘመን ፈጥሮበታል ። ባለፋት ሦስት ቀናት ውስጥ በጅጅጋና በሌሎችም የሶማሌ ክልል ከተሞች በአማራው ህዝብና በሌሎች ኢትዮጵያውያን ወገኖች ላይ የተፈፀመው ዘግናኝ ዘር ተኮር የጅምላ እልቂት በሊቢያ በረሀዎች ውስጥ በኢትዮጵያውያን ወጣቶች ላይ አክራሪ አሸባሪ ኃይል ከፈፀመው ጭፍጨፋ ጋር የማይተናነስ ሰዎችን ከነህይወታቸው ከዓብያተ ቤተክርስቲያን ጋር በእሳት እንዲነዱ ተደርገዋል ፤ ህፃናት ያለርህራሄ ተረሽነዋል ፣ ሴቶች በግፍ ተደፍረዋል ። ይህ በአማራው ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለው የማያባራው መከራ፣ ስቃይና የዘር ማጥፋት ወንጀል በተለይም በእርስዎ አስተዳደር ዘመን ውስጥ በመፈፀሙ ቀደም ሲል የሰነቅነው ተስፋችን ከመጨለሙም በላይ ከፍተኛ ድንጋጤን ፈጥሮብናል ። ሙሉወን ለማንበብ ይህን ይጫኑ።

Share this post