የመላው ዐማራ ሕዝብ ድርጅት (መዐሕድ ) የሐዘን መግለጫን ይመለከታል።

የተከበሩ የዐማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር ዶ/ር ገዱ አንዳርጋቸው ፣ ከሁሉ አስቀድመን ለርሶና ለለውጡ ኃይሎች ፣ የለውጡ ሂደት ደጀን የነበሩት የትግል አጋራችሁ አቶ ተስፋዬ ጌታቸው በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የብአዴን ማዕከላዊ ጽ/ ቤት ኃላፊና የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ‹‹አገሬ ሳትረጋጋ ጥያት አልሄድም ›› በማለት የህክምና ቀጠሯቸውን አሳልፈው ሄደው ህይዎታችው ማለፉን ዶክተር አምባቸው ለሀዘንተኞቹ እና ለሕዝቡ ግልጽ እንዳደረጉት ፡ የተሰማንን ልባዊ ሃዘን እንገልጻለን ። ለብአዴን የለውጥ ኃይሎችና ለቤተሰቦቻቸው መጽናናትን እየተመኘን፣ እግዚአብሄር የአቶ ተስፋዬ ጌታቸውን ነፍስ በአጸደ ገነት ያኖርልን ዘንድ ጸሎታችን እናደርሳለን።
መዐሕድ የአቶ ተስፋዬ ጌታቸው ሕልም ዕውን ይሆን ዘንድ ከለውጡ ኃይሎች ጎን በመቆም ለሕዝባችን ህልውናና ማንነት መከበር ፣ ለሰላምና ለጋራ ዕድገት እንደሚሰራ በድጋሚ ያረጋግጣል። መግለጫውን በ PDF ያንብቡ።

Share this post