መዐሕድ ራሱን ከአድማስ አገለለ።

መዐሕድ በቅርብ ጊዜ ውስጥ አድማስን ሲቀላቀል የተደረሰው የመግባቢያ መርህ የተለያዩ የአማራው የፓለቲካ ድርጅቶችን ፣የሲቪክ ማህበራትን ፣ የተለያዩ የብዙሀን መገናኛዎችን አሰባስቦ በጋራ የሚመካከሩበትና ለመጭው ትግል ዘመን በመደጋገፍና በማስተባበር እንዲደጋገፋ ታስቦ የተፈጠረ መድረክ ነበር ። ነገር ግን አሁን እየተደረገ ያለው ቀደም ሲል ሁላችንም ከተግባባንበት መርሀ ግብርና ስምምነት ውጪ አድማስ በራሱ እንደ አንድ የፓለቲካ ድርጅት በግሉ ውሳኔዎችን እየሰጠና እየተንቀሳቀሰ ይገኛል ።

መዐሕድ የአማራውን ህዝብ በትግሬ ወያኔ ከተጫነበት የግፍና የመከራ ቀንበር ለማላቀቅ በሚያደርገው ትግሉ ረጅም ጎዞ የተጓዘና በቆራጥ አማሮች ብዙ መስዋእትነትን የከፈለ የአማራው የነፃነት ትግል ፈር ቀዳጅ የበኩር ልጅ ነው ። ባለፋት 27 ዓመታት መዐሕድ በትግል የተፈተን የአማራው ህዝብ ለማንነቱ መከበርና ለነፃነቱ በሚያደርገው ትግል ጉልህ ስፍራ ያለው ለመሆኑ በአገር ቤት አባሎቹ የከፈሉት መስዋእትነት ለትግላችን የሚያጠነክሩን የማንነታችን ቋሚ አሻራዎች ናቸው ።

በተጓዝነው ረጅም የትግል ዘመን ፤ መዐሕድ ከሁሉም የአማራ ልጆችና ከተደራጁ የአማራ የፓለቲካ ድርጅቶች ፣በግል ከሚንቀሳቀሱ የአማራ አክቲቪስቶች ፣ ከታዋቂ አማሮችና ምሁራን ጋር በመተባበር በጋራ ለመስራት ወገናዊ ጥሪዎችን አቅርቧል ። ይህም እንዲሳካ በርካታ ጥረቶችን አድርጓል ።ለዚሁም ከአንድ ዓመት ተኩል በፊት የተፈጸመው ውህደት ትልቅ ማሳያ ነው ። በተመሳሳይ መንገድ መዐሕድ በአገር ቤትም ያሉት የአማራ ድርጅቶች ፣ የአማራ ምሁራን ፣ ሁሉም የአማራ ልጆች አንድ ሁሉንም የሚያሰባስብ የፓለቲካ ድርጅት / ፓርቲ እንዲመሰረት በመርሀ ግብር ደረጃ በመንቀሳቀስ ተግባራዊ እንዲሆን ይታገላል ያታግላል ።

በአሁኑ ሰዓት አድማስ እየተንቀሳቀሰ ያለው ከተስማማንበት ውጭ ውክልና ሳይኖረው አገራዊ በሆኑ የፓለቲካ ጉዳዮች ላይ አቋም በመውሰድና በመንቀሳቀስ ከመዐሕድ መርሀ ግብር ጋር የተፋለሱ ውሳኔዎችን በማውጣቱ መዐሕድ ከአድማስ ጋር ያለውን ግንኙነት ከዛሬ ሰኔ 27 ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ አቋርጧል። የመላው ዐማራ ሕዝብ ድርጅት ስብስቡ መንገዱ ሁሉ የተቃና እንዲሆንለን መልካም ምኞቱን ይገልጻል።

ድል ለአማራ ህዝብ!

የመላው ዐማራ ሕዝብ ድርጅት (መዐሕድ)

መግለጫውን በPDF ያንብቡ

Share this post