ከመላው ዐማራ ሕዝብ ድርጅት / መዐሕድ/ የተላለፈ የሀዘን መግለጫ

በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ለጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ ድጋፍ ለመስጠት በተሰበሰቡ ንጹሃን ዜጎች ላይ ጭካኔ በተሞላበት የቦምብ ትቃት ተፈፅሟል። ከሚመለከተው አካል የተገኘው መረጃም ከ 164 ያላነሱ ዜጎች እንደቆሰሉ እና አንድ ሰው እንደሞተ ያሳያል። ድርጅታችን መዐሕድ እንዲህ አይነቱን አስነዋሪ ድርጊት እንዲፈጸም ያቀዱ፤ ድጋፍ ያደረጉና በድርጊቱ የተሳተፉ አካላት በሙሉ ተገቢውን ቅጣት እንደሚያገኙ ተስፋ በማድረግ ለተጎጅ ቤተሰቦች መጽናናትን ይመኛል። የተሻለ ነገን በመናፈቅ በተሰባሰቡ ዜጎች ላይ የቆሰሉ ወግኖቻችን በቶሎ አገግመው ቤተሰቦቻቸውን እንደሚቀላቀሉ ድርጅታችን መልካም ምኞቱን ይገልጻል። ህዝቡም በአደጋው ሳይደናገጥ ለነጻነቱ የሚያደርገውን ትግል እንዲያፋጥን የመላው ዐማራ ሕዝብ ድርጅት ያሳስባል።  መግለጫውን በ PDF ያንብቡ።

ድል ለዐማራ ሕዝብ!

Share this post