በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከመላው ዐማራ ሕዝብ ድርጅት የተሰጠ መግለጫ

የትግሬ ህዝብ ነጻ አውጭ ግንባር (ትህነግ) ኢትዮጵያን በተቆጣጠረች ማግስት የአማራው ህዝብ ላይ በግልጽ የከፈተችውን የዘር ማጥፋት እና ማጽዳት ወንጀል ቀድመው የተረዱት ክቡር አባታችን ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ መዐሕድን በመመስረት በተለይም በምስራቁ የሃገራችን ክፍል ለሚገኘው አማራ ህልውና ቀድመው በመድረስ ወገናቸውን ታድገው አኩሪና አንጸባራቂ መስዋዕትነትን በመክፈል በክብር ካለፉ እነሆ አስራ ዘጠኝ አመታት ተቆጥረዋል። አስራት በቤዛነት በከፈሉት መስዋዕትነት በሚሊዮን የሚቆጠሩ አማሮችን ለመታደግ የቻሉ የቁርጥ ቀን አባታቸን ናቸው። በእርሳቸው የተለኮሰው የነጻነት ተጋድሎም ዛሬ በበረካታ ሚሊዮኖች ተቀጣጥሎ አማራ ለህልዉናው መከበር እና ለአስተማማኝ ደህነነቱ መረጋገጥ ሊቀለበስ በማይችል የሞትሽረት ትግል ውስጥ ተጠምዶ ይገኛል። ባስመዘገባቸው ድሎችም የነበረውን ሀገራዊ እና ዜጋዊ ከበሬታ በማስመለስ የተጋደሎውን አድማስ አስፍቶ ግስጋሴውን ወደፊት ቀጥሏል።ሙሉዉን ለማንበብ  እዚህ ይጫኑ ።

Share this post