ወጣት የአማራ መሪዎችን መታሰር አስመልክቶ አድማስ የሰጠው መግለጫ

በትግሬ ሕዝብ ነፃ አውጭ ግንባር(ትሕነግ) የሚመራው ዘረኛና ከፋፋይ፣ ፀረ-ኢትዮጵያና ፀረ-ዐማራ የሆነው ድርጅት የሚመራው ኢሕአዴግ ፣በ27 ዓመታት አረመኔአዊ አገዛዝ በአገሪቱ ብሔራዊ ጥቅም፣ ግዛታዊ አንድነት፣ በሕዝቡ አብሮነት ስሜት ላይ የፈጸማቸው አፍርሽ ተግባሮች ኢትዮጵያን እንደ አገር ልትቀጥል ወደ ማትችልበት አደገኛ አዘቅት ውስጥ እየከተታት እንዳለ ይታወቃል። ከዚህ አስከፊ የመበታተን እና የእርስ በርስ እልቂት መውጣት እንዲቻል፣ ዜጎች በዜግነታቸው፣ የፖለቲካ፣ የሲቪክ፣ የሙያ ማኅበራትና የብዙኃን መገናኛዎች አገሪቱና ሕዝቡ ከአስከፊ ጥፋት ራሳቸውን መከላከል እንዲችሉ በየፊናቸው የተቻላቸውን ሲያስተምሩና ሲመክሩ የነበሩና ያሉ ግለሰቦችን ከመግደልና ከማሰደድ የተረፉትን በሀሰት ክስ ወንጅሎ ለበርካታ ዓመታት አስሮ ማሰቃየቱ ይታወቃል።
አፈና፣ ግድያ፣ እስራትና ሥቃይ የበዛበት ሕዝብ በአፋኙና በገዳዩ ላይ ማመጽ ተፈጥሮአዊ ግዴታ በመሆኑ፣ የትግሬ-ወያኔ(ትሕነግ) የጫነበትን የመከራ ቀንበር ሰባብሮ ለመጣል ሕዝቡ ፣ባገኘውና በመሰለው መንገድ በተናጠልና በቡድ ባቀጠጣለው ሕዝባዊ አመጽ: የአፋኙ አገዛዝ የአፈና እና የግድያ መዋቅሩ ከሥሩ በመናጋቱ፣ ከሁሉም በላይ ደግሞ አማራው ብሄርተኝነቱን አጠናክሮ ብሄሩን መሰረት አድርጎ በፖሊሲ ደረጃ ተቀርጾ ሊያጠፋው የመጣውን ጠላት ለመከላከል በየአለበት ከመደራጀት ጀምሮ እስከ ነፍጥ አንስቶ በመታገል ህልውናውን ለማስከበር ቆርጦ በመነሳቱ ፣ ወያኔ የቆመበትን ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ መሠረት ከሥሩ አናጋው… ይህን ይጫኑ ።  Click Here to read English version of the press release.

 

Share this post