በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከመላው ዐማራ ህዝብ ድርጅት የተሰጠ መግለጫ

በወቅታቂ ጉዳዮች ላይ ከመላው ዐማራ ሕዝብ ድርጅት የተሰጠ የአቋም መግለጫ

ጳጉሜ 3 2009 ዓ.ም

አንድ ስንዝር መሬት ከዐማራው ታሪካዊ ቦታዎች ላይ ለማንም ተላልፎ አይሰጥም!
ወልቃይት ጠገዴ-ራያ-መተከል ትናንትም ዛሬም ዐማራ ነው!

የዐማራ ሕዝብ እና የቅማንት ማህበረሰብ ለዘመናት ሳይነጣጠሉ ማህበራዊ እሴቴቶቻቸውን እየተጋሩ አብረው ኖረዋል። በደስታቸው ወቅት አብረው ተደስተው በሃዘናቸውም ጊዜ አብረው አዝነዋል። እርስ በርሳቸው የጋብቻ ትስስርን ፈጥረው ልጆችን በጋራ አፍረተዋል። አገራቸውን በህብረት ከጠላት ወረራ ተከላክለዋል። ለዚህ ማስረጃ ከቢትወደድ አዳነ አባደፋር ጎን ተስልፎ ጣልያንን የወጋው የፊታውራሪ አየለ አባጓዴ የአረበኝነትን ተጋድሎ መጥቀስ በቂ ነው። የዐማራ ሕዝብ ያለውን ባህላዊ እሴቶች ሁሉ የቅማንት ማህበረሰብ ይጋራል። ዐማራን ዐማራ የሚያሰኙት ነገሮች ሁሉ በቅማንቱም ላይ አሉ። የቅማንት ማህበረሰብ ትናንት በትግሬ መራሹ አገዛዝ አልተፈጠረም። የቅማንት ማህበረሰብ ትናንትም አለ ነገም ይኖራል። የአማራ ሕዝብ ለቅማንት ማህበረሰብ የዘመናት አጋሩ ወንድሙና አብራኩ እንጅ ጠላቱ ሆኖ አያውቅም።

“የቅማንት የማንነት ጥያቄ” ስያሜን የተሰጠው ስውር ሴራ “የታላቋ ትግራይ” ምስረታ ሂደት አንዱ አካል ነው። ያ ማለት ግን ቁጥራቸው ጥቂት የማይባል ስልጣን ፈላጊ የቅማንት ተወላጆች ከጉዳዩ ጀርባ የሉም ማለት አይደለም። ከማንነቱ እና ከግዛት ይገባኛል ጥያቄው ጀርባ ካድሬዎችን ከማሰልጠን እስከ የአማራን ጥላቻ መዝራት ሌት ተቀን የሚታትሩ የትግሬ ተስፋፊዎች አሉበት። ከማንነቱ ጥያቄ የቅማንት ማህበረሰብ የሚጠቀመው አንዳች ነገር የለም ብለን እናምናለን። በስተመጨረሻ ያለምንም ኪሳራ ተጠቃሚነቱን የሚወስዱት የትግራይ ተስፋፊዎች ናቸው። የዐማራ ሕዝብ እንደ ሕዝብ ማንኛውንም ሕዝብ አልበደለም። ከአንዳንድ በህወሃት በሰለጠኑ ስልጣን ፈላጊ የቅማንት ተወላጆች የሚናፈሰው የበደለኝነት ስሜት ከሃቅ የራቀና ከህወሃት የአዕምሮ እጥበት ጋር የሚያያዝ ነው። የህወሃት አላማው አንድ ነው፤ እሱም በፍኖተ መርሁ በግልጽ እንደተቀመጠው በዐማራው መቃብር ላይ “የታላቋን ትግራይ” መመስረት ነው። ይህ ለቅማንት ማህበረሰብም አደገኛ ነው። ዛሬ ላይ አጋር መስለው የቀረቡ ቢመስሉም ኋላ ላይ ግን የተንቤን አገዎችን፣ የሳሆዎቹን፣ የኩናማዎችን እጣ ፋንታ በቅማንቱም ላይ መጫናቸው አይቀርም። … Read more በወቅታዊ-ጉዳዮች-ላይ-ከመዐሕድ-የተሰጠ-መግለጫ

Share this post