የዳግማዊ መዐሕድ እና የቤተ-ዐማራ መድህን ውህደት አስመልክቶ ከዐማራ ማህበር በጀርመን የተሰጠ የድጋፍ መግለጫ

የዳግማዊ መዐሕድ እና የቤተ-ዐማራ መድህን ውህደት አስመልክቶ ከዐማራ ማህበር በጀርመን የተሰጠ የድጋፍ መግለጫ

በትናንትናው እለት ኦውገስት 20 2017 ዓ.ም የሁለቱ ድርጅቶች ውህደት ዜና በመስማታችን ደስ ብሎናል። የህዝባችንን ጥያቄና የልብ ትርታ አዳምጣችሁ ምላሽ በመስጠት ረገድ ፈር ቀዳጅ በመሆናችሁ እናደንቃለን። እስካሁን ላሳያችሁት ህዝባዊ ወገንተኝነትና የትግል አስተዋጽኦም አክብሮት አለን። ይበልጥም አሁን ባሳያችሁት ቁርጠኝነትና በወሰዳችሁት የውህደት አቋም ኮርተናል። እንኳን ለዚህ አበቃችሁ እንላለን።

አንድነቱን ያልጠበቀ ሕዝብና እራሱን የማይከላከል ትግል እርባና የለውም። ስለሆነም ዐማራ አንድ ሕዝብ ነው። በታሪኩም የሚከበር፣ በማንነቱም የማያፍር፣ በባህሉም የሚዘከር፣ በነቃ ስነ-ልቦና የሚኖር፣ በሃይማኖቱ የማይደራደር፣ በሃገሩና በነጻነቱ የሚታፈር፣ ሁሉን አክባሪና አሳታፊ፣ ህዝባዊ ልዕልና ያለው፣ በራሱ የሚተማመንና ፈጣሪውን ብቻ የሚፈራ ኩሩ ሕዝብ ነው። ከዚህ ዘውግ በመወለዳችን ክብርና ኩራት ይሰማናል።

የዐማራ ሕዝብን መብትና ታሪካዊ ማንነት ለማስከበር በሚደረገው በዚህ እልህ አስጨራሽና መራራ ትግል ቀዳሚውን ረድፍ በመያዝ ከአምባገነን ፋሽሽት ወያኔና ዘረኛ ቡድኖች ጋር ፊት ለፊት ከገጠመው ወገናችን ጎን አጋር በመሆን ለቆማችሁ ሁሉ ዛሬ በዳግማዊ መዐሕድ እና በቤት-ዐማራ መድህን የተወሰደው የውህደት እርምጃ ተስፋ ሰጭና በእጅጉ የሚያኮራ ተግባር ነው።

ይኸው ጅምር በቀጣይ ተጠናክሮ ከሌሎች የዐማራ ድርጅቶች ጋር በተመሳሳይ ሁኔታ በመግባባት ወደ ውህደት እንዲሸጋገር ጽኑ ምኖታችን ነው። በመሆኑም ሁሉም የዐማራ የፖለቲካ ድርጅቶች በአንድ የፖለቲካ ማእቀፍ ውስጥ በመሰባሰብ ጠንካራና ህዝባዊ መሠረት ያለው የፖለቲካ ሃይል እንድትመሠርቱና ትግሉን በብቃትና ባስተማማኝ እንድትመሩ በማለት በዚህ አጋጣሚ በአክብሮት ጥሪ እናቀርባለን።

ዐማራውን ለማደራጀትና ትግሉን አቀናጅቶ በብቃት ለመምራትም ሆነ ለመዋሃድ የምታደርጉት ሁለገብ ጥረት እንደ አንድ የዐማራ ቤተሰብ ከጎናችሁ እንደምንቆም ልንገልጽላችሁ እነወዳለን።

ዐማራነት ክብራችን ነው!
የዐማራ ብሄርተኝነት ይለምልም!

የዐማራ ማህበር በጀርመን
ኦውገስት 21 2017

Share this post