የአማራ አለማቀፍ ጉባኤ ከብር ኢዮቤልዮው ክብረ በዓል ጋር በዲ.ሲ. May 14/2017

የአማራ አለማቀፍ ጉባኤ ከብር ኢዮቤልዮው ክብረ በአል ጋር በዲ.ሲ. May 14/2017

1. ታላቁ የአማራ አለማቀፍ ጉባኤ May 14/2017 በዋሽንግተን ዲ.ሲ. ይካሄዳል፡፡
2. የመላው ዐማራ ሕዝብ ድርጅት 25ኛ አመት የብር ኢዩቤልዮ በዓል ተከብሮ ይውላል፡፡
3. የፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ 18ኛ አመት ሰማእትነት መታሰቢያ እለት ታስቦ ይውላል፡፡
4. የዳግማዊ የመላው ዐማራ ሕዝብ ድርጅት እንደገና ምስረታ 2ኛ አመት ይዘከራል፡፡
5. የአማራ ህዝብ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ የድንበርና የደህንነት ጥያቄዎችን የሚያካትተው የአማራ ሰነድ ዝግጅት ይደረጋል፡፡ ለፌብሯሪ 18/2017 ተይዞ የነበረው ይህ ዝግጅት በተለያዩ የፕሮግራም መደራረቦች ምክንያት ከመዐሕድ ብር ኢዩቤልዮ ጋር ተሸጋሽጎ እንዲከበር ተወስኗል፡፡ ከተለያዩ ምሁራን የሚቀርቡት ጽሁፎች በቂ የጥናት እና ምርምር እንዲሁም የዝግጅት ጊዜ እንዲኖራቸውም ያስችላል፡፡

ይህንን የአማራ አለማቀፍ ጉባኤ በትብብር ለማዘጋጀት የምትፈልጉ የአማራ ድርጅቶች ፍላጎታችሁን በድርጅታችን Email: AAPO2nd@gmail.com እንድታሳውቁን ስንል በትህትና እንገልጻለን፡፡

ዳ/መዐሕድ

Share this post